ቅድስት ናት ለዘለአለም
በልቤ ውስጥ እንዲታተም
የልጅሽ የኢየሱስ ህማም
የሐዘን እናት የእባ ባህር
ቁማ ነበር እመስቀል ሥር
ተቸንክራ በፍቅር
ከባድ ሀዘን የተጫናት
ነፍሷን ቦታ የጠበባት
የሀዘን ሰይፍ የወጋት
ወይ የጭንቅሽ የእንባሽ ባህር
መጠን የለው ሥፍር ቁጥር
ቅድስት የአንድ አምላክ ወንበር
ምን ይመስል ሀዘንሽ
ከመስቀሉ ያ ልጅሽ
ቁልቁል አንቺን ሲያይሽ
ማነው ከኛ እሷን አይቶ
ያንን ጭንቋን ተመልክቶ
እንባ የማይወጣው ከቶ
ማነው ከኛ ሳያዝንላት
ደፍሮ ጭንቋን የሚያይላት
ለዚያች ለአንድ አምላክ እናት
ስለሕዝቡ ኃጢያት
ኢየሱስን ሲገርፉት
ታይው ነበር በጭንቀት
ያንን ልጇን ወዳጇ
እመስቀል ላይ ድካሙን
ታይው ነበር ሞቱን
ካንቺ ጋር እንዳነባ
የንቺ ሀዘን ልቤ ይግባ
ቅድስት የፍቅር አበባ
ልቤ እንደ እሳት እንዲቃጠል
ኢየሱስን በማገልገል
አማልጂን ቅድስት ድንግል
አንዱ ልጅሽ የሞተልን
ያለመጠን የወደደን
ሕማሙ ሕማም ይሁነን
ላልቅስ ላልቅስ ከአንቺ ጋር
ነፍሴ ላለች ሣላባራ
ስለ ክርስቶስ መከራ
እመስቀል ስር የተገኘው
ከአንቺ ጋር ባለቀስኩ
በደም እምባ በታጠብኩ
የደናግል ሁሉ ድንግል
እንባ ይመጣ ሰለአንቺ ስል
ስለ ልጅሽም መስቀል
ሸከም ይሁን የአምላክ ሞቱ
ደግሞ ርስቴ ሕማማቱ
ትዝታዬም ግርፋቱ
አበሳዬ ለዚያ ለእሣት
አሳልፎ እንዳይሰጣት
ድንግል ነፍሴን ታደጊያት
ነፍሴ ከሥጋ ስትወጣ
ኢየሱስ ሆይ ደጉን ዕጣ
ስለእናትህ እንዳላጣ
ስበሰብስ አፈር ስሆን
የነፍሴ ረስት ገነት ይሁን
ኢየሱስ አደራህን
