ቃልኪዳን ገባሁኝ ከወዳጄ ጋራ ካባብዬ ጋራ
በስምህ ልጠራ ስምህን ላስጠራ ቃልኪዳን
ገባሁኝ ከወዳጄ ጋራ /2/
ማለዳ ማለዳ አሀሀ ድምፄን አስማለሁ
በንጋት በምሽት እህህ ፊትህ እቆማለሁ
በምህረትህ ብዛት ወደቤትህ ገባሁ
አንተን ተማምኜ /2/ አንተኑ ታምኜ
አለምን አሸነፍኩ
ተማምኛለሁ ስራህን አውቃለሁ
ተማምኛለሁ ምህረትህ ብዙ ነው
ተማምኛለሁ ስትረዳኝ አውቃለሁ
ተማምኛለሁ አስተማማኝ ነው
የፊትህ ብርሃን አሀሀ በላዬ ላይ ይብራ
በመላው አካሌ ኤሄሄ መንፈስህ በኔ ይስራ
ጨለማን አልፈራም ብርሃን ነው ውድዬ /2/
መንገዴን ሰጠሁኝ ታማኝ ነህ ጌታዬ
አስጨናቂዎቼ ኤሄሄ ኧረ እንዴት አፈሩ
መድሃኒቴ ጠራኝ አሃሃ የኛ ነው እያሉ
አልፈራሁም እኔ ጠላቴን ፈርቼ
ሰማሁኝ ሲጠራኝ ጌታዬን ወድጄ
ፍቅሩ እየሳበኝ ጌታዬን አመለኩ
ስጋዬን ሲበሉ ነፍሴን ግን አስመለጥኩ
አምልጬዋለሁ ስትጠራኝ አውቃለሁ
አምልጩጬዋለሁ ምህረትህ ብዙ ነው
አምልጬዋለሁ ዳግም ላልመለስ
አምልጬዋለሁ ቃልኪዳኔን ላድስ
