መድኃኒቴ ነህ መድኃኒቴ የሱስ ለሕይወቴ
በአንተ እኮ ነው መውጣት መግባቴ መድህን ብርታቴ /2/
1. ችግር መከራ ተፈራርቆብኝ
የማማክረው በሙሉ ታክቶኝ
ሁሉም ሰልችቶኝ በሰው ተንቄ
ጌታ አልተውከኝም አንተ በችግር ጭንቄ
2. ማዕበሉን ሁሉ ጸጥ የሚያደርገው
ባህሩንም ከፍሎ የሚያሻግረው
የፍቅር አምላክ ድንቅ አድራጊ ነው
ወዳጅ ላጣችሁ ወዳጅ የሱስ ነው
3. ያድነኛል ብል ከሰው ዘንድ ብሄድ
ማንም አልቻለም እኔን ሊፈውስ
ፈውስ ከአንተ ካልሆነ በቀር
አላገኘሁም በሽታን ሚሽር
4. ተአምር ሰሪ የተግባር አምላክ
እኔን ባሪያህን በፍቅር የማረክ
የምትከልለኝ ረዳቴ የሆንክ
እዳዬን ከፍለህ ፍርዴን ተቀበልክ
