ማርያምን ለማብሰር እግዜር የመረጠህ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ አይለየን እርዳታህ
ፈጥነህ አምጣልን የምስራቹን
የሚያበስረውን መዳናችንን
1. ሰዎችን ለማዳን በሚስጥረ ስጋዌ
ነፃ እንድንሆን ከዓለም ክፉ ደዌ
ለዚህም መሳካት አንተ ተመርጠሀል
ማርያምን አብስር ብሎ እግዜር መርጦሀል
2. ደስታን ስታበስር በምድረ ገሊላ
መልዕክት ስትቀበል ማርያም እሺ ብላ
እንደተጎናፀፍከ ሰማያዊ ደስታ
እንደማርያም አርገን በዘካሪያስ ፋንታ
3. አስቸጋሪውን ራዕይ በፊቱ ተረጎምክ
ማስተዋል ጥበብን ለዳንኤል አስተማርከ
እኛንም እባክህ በክንድህ እቀፈን
እግዜርን እንድናመልክ ማስተዋልን ስጠን
