ትሲቴ ታላቅ ነው አመፃን ለብሻለሁ
በሐጥያቴ ብዛት ስንቴ ወድቄአለሁ
ጠፍሮ የያዘኝ እረ እርሱ እረ ማነው
ማየት እስኪሳነኝ እይኔን የጋረዳው
አዬ አዬ ብለህ እያዘንክ ጌታዬ
ስንቴ ገሰፅከኝ ከክፉ ስራዬ/2/
ዝላዩ ጭፈራው እኔኑ እያሞካሸኝ
በየት በኩል ልውጣ የሙጥኝ እየያዘኝ
ላታላዩ አለም ስጋዬን በጣም አድሏታል
አንድ ቀን መድከሙን ጭራሹን ዘንግቶታል
የሚታየኝ እሩጫ ሁሌ ለግዚያዊ ደስታ
ነፍሴ እረፍትን አጣች መንገዷንም ስታ
ብዙ ጊዜ ሆነኝ ቃልህን ትዛዝህ ንቄ
መቼ ነው የምገኘው ከሃጥያት እርቄ
ክበር ክበር ጌታ በመላው ገላዬ
ሰደሌን ሳይቆጥር ሽሮታል እዳዬን
ብርሃን ከጨለማ ፍፁም ልዩነት እንዳለው
አሁን ነው የምረዳው አንተን እንዳገኘው
ለምን ዘገየብኝ ብዬ ዳግም እርሱን ስከስ
ሐጥያቴን የማረኝ አረሳው ላስታውስ
