ማርያም የፍቅር እናት

216

ማርያም የፍቅር እናት እኛ እንወድሻለን
በዘመናችንም ቃልኪዳን እንገባለን
እየሱስ ነግሮናል እንቺን እንድንወድሽ
ልባችን ከፍተን በውስጥ ልናኖርሽ

እንከን አይወጣለት ለእናትነትሽማ
ጌታሽ አጠባሽ ለራሱ አላማ
መታዘዝስ ቢባል ትህትናሽ የላቀ
እጣው እንደው ምን ይሆን አንቺን ያላወቀ

እኛስ ታድለናል በህይወታችን ዘመን
እናት ልትሆነን ማርያምን አገኘን
ኢየሱስ አንዳለሽ ይኸውልሽ ልጅሽ
ወደ አባታችን ምሪን በፍቅርሽ

ፍፁም እንከን የለሽ ከሐጥያት የነፃሽ
ትዕዛዝ መተላለፍ የሆነው ያልነካሽ
ልጅሽ የኛ አባት ይርዳን በምሕረቱ
እኛ እንወድሻለን ንገሪው ንፅእቱ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top