አመፀኛዋን እኔን ወደደ
ለዚህም ከሰማያት ወረደ
በመስቀል ጣር እስከሞት ሄደ
አረጋጋኝ ልቤን ካራደ
አሳረፈኝ ልቤን ካራደ
ይኸው ማርያም ይህ በኩርሽ
ህይወት ሆኖኝ ዛሬ ልጅሽ
ለካ እንዲህ ነው የወደደኝ
እሰኛለው እሱ አከበረኝ
ለዚህም ነው ያፈቀረኝ
ከራሱ ጋር ሊያኖረኝ
ማርያም ያ አንዱ ልጅሽ ካለመጠን ወዶኝ
ፍቅሩን ሰጠኝ አዝኖና ራርቶልኝ
ራሱን ሰጠኝ ከሞትም አዳነኝ
ሀብታም ደሀ ያላለ ፍቅር
በተግባር የታየ ምስክር
ባንዱ ልጅሽ በየሱስ ብቻ / ባምላኬ ብቻ
ይህን አየሁ ፍቅር ትርጉም መፍቻ
ትምህርት አየሁ
ኦ ድንግል ሆይ ይህ ማህፀንሽ
ስጦታውን ሰጥቶኝ ፍሬሽ
አይወሰድ ከኔ ዘላለም
በዚህም ቢሆን በመጭውም አለም
