የጌታን ፊት ተመልክቶ መኖር የሚችል
ከቶ የለም ከፍጥረት
በግርማው ፊት በፀባኦት በፍርሃት የሚቆሙ ቅዱስ ነህ እያሉ
ማርያም ግን ከዚህ ሁሉ ተለይተሻል
መለኮትን ይዘሻል
ከማየትም ፀንሰሽዋል እንድናየው ምክንያት ሆነሻል ድንቅም ሆኖልሻል
ማርያም ማደሪያው የአምላክ ማርያም /2/
የእ/ር ቅዱስ ቃል በድንጋይ ተቀረፀ በጽላት
በታቦትም ተቀመጠ ለእስራኤል ድንቅ አደረገ
መንፈሱም መራቸው
የእ/ር ቃል ስጋ ለብሶ ተገለጠ በማርያም ተቀመጠ
ወንጌልንም ሰበከ ደዌን ሁሉ ፈወስ መንፈስም ሰጣቸው
እ/ር ፅዮንን መርጧታል ማደሪያውም እንድትሆን
ህዝቦች ሁሉ ኑ እንሂድ ወደፅዮን ወደእርሱ ቤት በረከት ለማግኘት
እ/ር ማርያምን መርጧታል ማደሪያውም እንድትሆን
ህዝቦች ሁሉ ኑ እንሂድ ወደማርያም ወደእመቤት በረከት ለማግኘት
የልዑል ሃይል አንቺን ጋርዶ ፀልሎሻል
መንፈስ ቅዱስ ሰርቶልሻል ጌታ ኢየሱስ ባንቺ አድሮአል
ሥላሴ ባንቺ ተገልጧል በማርያም ድንቅ ሆኗል
