ምስጋና ለጌታ

151

ምስጋና ለጌታ መልካም እረኛችን
ሕይወቱን ሰውቶ ሆኗል ቤዛችን
ደግ እረኛ ነው ትቶልናል ካህናት
ለነፈሳት ጥበቃ ለስርየት ሐጥያት

ሥጋውን ፈትቶ ሲያዝዝ ለመብላት
እንካፈልም ዘንድ ከመለኮት ሙላት
ይህን ድንቅ ተአምር የጥልቅ ፍቅር ሥርዓት
ትቶልናል ራሱ በሥልጣነ ካህናት

እፍም አለባቸው ለሐዋሪያት ግቡአን
ሥልጣን ተቀብሎ ለምህረተ የጢአን
ሐጥያትን የመሰረይ አምላካዊ ስልጣን
ምሕረት የተሰጠ በአዲሱ ኪዳን

እናንተን የሚሰማ እኔንም ይሰማል
ብሎ ወከላቸው በምስራቹ ቃል
ሉቃስ ወንጌላዊ ብሎ መስክሮአል
የሰማያት ቁልፍ ለነሱ ተሰጥቷል

ሃሌሉያ ለአብ ለቸሩ አምላክ

ሃሌም ደገመ ለወልድ ለመድሃኒታችን
ሃሌሉያ ለአፅናኝ ለነፍሳችን ቀዳሽ
/ካህን/ ጳውሎስ ቀብቶልናል
የጴጥሮስን ወራሽ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top