እግዚአብሔር ግሩም ነህ
ድንቅ ነህመልካም ነህ
በእውነት አንተ ነህ ምስጋና የሚገባህ
ክብር የሚገባህ
አምላክ ጌታ ነህ
ድንቅ ነህ መልካም ነህ /2/
ሰልፈኞች ተነስተው እጅግ አስጨነቁን
ማዕበል አስነስተው ሊያስምጡን ሊያጠፋን
ለኛም እጅግ ፈርተን ወደ አንተ ስንጮህ
ማዕበሉን ፀጥ አረከው ጩኸታችንን ስምተህ
የሠራዊት ጌታ ምሥጋና ይድረስህ /2/
እኔ ታላቅ ሰው ነኝ ብለው የተነሱ
ጠፉ እነቲዎዶስ አልቻሉም ሊነግሱ
አንተ ግን አንተ ነህ የነበርክም ያለህ
ለዘላለም ምትኖር ጊዜ ማይለውጥህ
ሠራዊት ጌታ የለም የሚመስልህ /2/
ለቁጣ የዘገየህ በፍቅር የተሞላህ
ከስሞች ሁሉ በላይ ታላቅ ስም ያለህ
አንተ ከተቆጣህ ማን ፊትህ ይቆማል
ሰይፍህ ነቅነቅ ካለ እልፍ ሺ ይጥላል
የኛ አምላክ እግዚአብሔር ጀግና ነው
እጅግ ኃያል /2/
ሕዝብህን ከፈርኦን ባርነት የታደግህ
ጭው ባለ በረሃ ምንጭን ያፈለቅህ
ባሕሩንም ከፍለህ በድንቅ እየመራህ
የተስፋይቱን ምድር ከነዓንን አወረስህ
ለዚህ ሁሉ ውለታ ምን አለን ምን
እንከፍልህ
ክበር በቃ እንበልህ
