ምስጋና

90

መልካምን አድርገሃል ለኔ
ስትረዳኝ አይቻለሁ በአይኔ
ውለታህ እኔ አለብኝና
ቆሜአለሁ ፊትህ በምስጋና
ምስጋና /3/ አምላኬ ይገባሃልና /2/

ለኔ ያደረከው ግሩም ነው ድንቅ ነው
ካይምሮዬ በላይ በቃልም አልገልፀው
ለውለታህ ምላሽ እኔ አለኝ የምለው
ሌላ ነገር የለኝ ምስጋና ብቻ ነው

መልካምነትህን ችዬ ምገልፅበት
አንድም ቃላት የለኝም የምመጥንበት
ግን እኔ አልሻም ማለፍ በዝምታ
አመስግን ይለኛል ለበዛው ውለታ

ምስጋና /3/ ይገባሃልና

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top