ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና
ለሊትም እንደ ቀን ታበራለችና .አሃሃ
ስራህን ግን ነፍሴ እጅግ ታውቀዋለች
ማለዳ ተነስታ ክበር ትልሃለች . አሃሃ
ምስጋናዬ /2/ በየለቱ ይድረስህ ጌታዬ
አምልኮዬ /2/ በየለቱ ይድረስህ ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ማንስ ይመስልሃል
ሰማይና ምድርን በቃልህ ፈጥረሃል . አሃሃ
ውበትህ ያማረ ግርማህ አስፈሪ ነው
ጉልበትህ አይዝልም ዘላለማዊ ነው . አሃሃ
ነገስታት ያልፋሉ ደግሞም ያረጃሉ
አለምም ሞላዋን ሁሉም ይጠፋሉ አሃሃ
አንተ ግን ህያው ነህ ዘለአለማዊ ነህ
በማደሪያህ ሁሌ ፀንተ ትኖራለህ .አሃሃ
አንተ ልዩ ነህ የኔ ጌታ /2/
አንተ ፍቅር ነህ የኔ ጌታ /2/
አንተ ትልቅ ነህ የኔ ጌታ/2/
