ምኔን አይተህ ነው ጌታ ምኔን
ምኔ ስቦ ነው ኢየሱስ የኔ
በዘላለም ፍቅርህ እንዲህ ያፈቀርከኝ
ውርደቴን ለውጠህ ወዳጅህ አረከኝ
አንተ ግን /3/ ልዩ ነህ
ሀሳቤ ጠማማ ለማንም ማይመች
ልቤም ክፉ ሀሳቢ መልካሙን አሳሳች
ኃላፊውን ደስታ ጊዜያዊውን ተመልካች
አንተ ግን ልዩ ነህ አዲስ ሰው አረከኝ
አመሌን ለውጠህ ፍቅርህን ለገስከኝ
ጊዜያዊ ምኞትን ምርኩዜን አድርጌ
ፍፁም ተድላንና እርካታን ፈልጌ
ቁምነገሩን ተውኩት ደንቡን ብቻ አክብሬ
አንተ ግን ጌታ ሆይ ፍፁም አልተወከኝም
ምስቅልቅል ሕይወቴን ልትነፍገኝ አትወድም
