ገባኝ አምላኬ አሁን ገና ገባኝ /2/
ለመልካም ነው እኔ ሳላፈቅርህ እንዲሁ ያፈቀርከኝ
ለመልካም ነው ለበጎ ዓላማ ነበር የምትሻኝ
ለመልካም ነው ባላሰብኩት መንገድ በድንቅ የጠራኸኝ
ትንሽዋ ጎጆህን ትተህ ሂድ ስትለኝ
ወደ ሰፊው ቤትህ ደግሰህ ስትጠራኝ
አይገባኝም ነበር ይህ በጎ ዓለማህ
ለካስ ልታደረገኝ ነው የሠላም መሣሪያህ
ደጋግመህ ስትጠራኝ በለስላሳው ድምፅህ
መልሴን ስትጠብቅ አቤት እንድልህ
ስታስተምረኝ እኔም እንድጣራ
አይገባኝም ነበር ይህን ሁሉ ሥትሠራ
እኔ ሳልፈልግህ ፈልገህ ያገኘኸኝ
ከተያዝኩበት ጭቃ ስበህ ያወጣኸኝ
ከዚያ ከነጣቂው ተኩላ አፍ ያዳንከኝ
ለበጎ እንደምትሻኝ አሁን ገና ገባኝ
እፊት ፊቴ ቀድመህ እኔን ስትመራኝ
ይህ ቀና መንገድ ይሻላል ስትለኝ
ብዙ ስትሻኝ እኔን ልጅህን
አላየሁም ነበር ረቂቅ ሚስጢርህን
ጠላት በዓይነ ቁራኛ ሲከታተለኝ
ግራ ቀኝ ሆነህ በሠራዊትህ ያጀብከኝ
ዘወትር ሳትዘነጋኝ የተጠነቀክልኝ
ለካስ ለመልካም ነው እንዲህ የምትሳሳልኝ
