ምድርም ትናገር

-

አዝ. ምድርም ትናገር ሰማይም ይመስክር
ማነው እንዳንተ ጌታ ሁሉን የሚችል
ፍቅርህን ያዩ የቀመሱት ሁሉ
ዛሬም ለክብርህ ቆመው እልል ይላሉ
ይኸው በቤትህ ሆነው ተመስገን ይላሉ

1. ጥበበኛ አምላክ የጥበብ ባለቤት
የማትሰለች ነህ ቀንም ሆነ ለሌት
ዙሪያችንን ሁሉ በደምህ አጥረሀል
አንተ ክበርልን አሜን ክብር ይገባሀል/2/

አዝ. ምድርም ትናገር ሰማይም ይመስክር
ማነው እንዳንተ ጌታ ሁሉን የሚችል
ፍቅርህን ያዩ የቀመሱት ሁሉ
ዛሬም ለክብርህ ቆመው እልል ይላሉ
ይኸው በቤትህ ሆነው ተመስገን ይላሉ

2. የሰማዩ ንጉስ የሰማዩ አምላክ
መንፈስህን ላከው እኛም እንባረክ
ይጠንክር ክንዳችን ልባችንም ይፅና
ማራናታ ብለናል እኛም ጌታ ሆይ ቶሎ ና/2/

አዝ. ምድርም ትናገር ሰማይም ይመስክር
ማነው እንዳንተ ጌታ ሁሉን የሚችል
ፍቅርህን ያዩ የቀመሱት ሁሉ
ዛሬም ለክብርህ ቆመው እልል ይላሉ
ይኸው በቤትህ ሆነው ተመስገን ይላሉ

3. ባንተ እናያለን ገና ብዙ ብዙ
ተስፋ ጥለን እኛም እናልፋለን ወንዙ
ወራሾች አድርገህ ሾመኸናልና
እናከብርሀለን አንተን ሁሌ በምስጋና/2/

አዝ. ምድርም ትናገር ሰማይም ይመስክር
ማነው እንዳንተ ጌታ ሁሉን የሚችል
ፍቅርህን ያዩ የቀመሱት ሁሉ
ዛሬም ለክብርህ ቆመው እልል ይላሉ
ይኸው በቤትህ ሆነው ተመስገን ይላሉ

4. በርትተናል ባንተ ፍቅርህን ቀምሰን
ወዴት እንሄዳለን ከአንተ ርቀን
አያይዘወኸዋል እጃችንን ሁሉ
ተዋደናል ባንተ ጌታ ልጆችህ በሙሉ/2/

አዝ. ምድርም ትናገር ሰማይም ይመስክር
ማነው እንዳንተ ጌታ ሁሉን የሚችል
ፍቅርህን ያዩ የቀመሱት ሁሉ
ዛሬም ለክብርህ ቆመው እልል ይላሉ

የምስጋና
Amharic
St.Gabriel

Leave a Comment

Scroll to Top