ራራልኝ

55

ራራልኝ አዘነልኝ
እኔ ከምሞት እርሱ ሞተልኝ/2/
ህይወቱን ሰዋልኝ
እንዴት ያለ ፍቅር ነው
እንዴት ያለ መውደድ ነው
ኢየሱስ ለእኔ የገለፀው

በደል ሃጥያቴ እጅግ በዝቶ
አንዳችም ነገር የሚያፅናናኝ ጠፍቶ
ከሰማይ ሰማይ ኢየሱሴ ደርሶ
ነፃ አወጣኝ ደሙን አፍስሶ

የከበረ ነው የእኔ ዋጋዬ
በደሙ የገዛኝ ውዴ ጌታዬ
ሃፍረት የለብኝ አልሸማቀቅ
አለቃ ጠበቃ አልጨናነቅ

የሚያደንቀኝ የፍቅሩ ፅናት
እስኪሞት ድረስ ነፍሴን ወደዳት
ዘመኔን ሁሉ እገረማለሁ
ፍቅር እንደርሱ የለም እላለሁ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top