ልግባ ወደ እልፍኜ

56

እስቲ ልሂድና ልግባ ወደ እልፊኜ
ላጫውተው የልቤን ሁሉንም ዘርዝሬ

በጠላቴ ሤራ ፈዘዙ ዓይኖቼ /2/
ከአቅሜ በላይ ሆኖ ዛሉ ጉልበቶቼ /2/
መሸከም አቃተኝ ከብዶኛል ልበለው
የሚያስጨንቀኝን ዘርዝሬ ላጫውተው

አምናለሁ አምላኬ ቀርቤ ባዋየው /2/
ቁስሉ ጫንቃዬን እንደሚፈውሰው /2/
ያቃልልልኛል ቀርቤ ባዋየው
ቀንበሩ ልዝብ ነው ሸክሙም ቀላል ነው

ኃያል ነው አምላኬ የለም የሚሣነው /2/
ያበረታኛል ዛሬም እንደ ትናንትናው /2/
ሚስጥረኛዬ ነው ችግሬን ይረዳልኛል
ሀዘኔን ለውጦ ደስታን ይሰጠኛል

የእኔ ከንቱ መድከም የለውምና ፍሬ /2/
ልግባ ወደ እልፊኜ እርሱን ተማምኜ /2/

ችግሬን ሊያቃልል አልቻለም ማንም ሰው
ከእንግዲስ ተስፋዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top