ራስህን ለውጥ

168

ከዓለም ጋራ በመሆን ኣታጥፋ ጊዜህን
መለወጥ ያሻሃል መርምር እራስህን
በጾም በሱባኤ እራስህን ለውጥ
የእግዚአብሔር ምህረት በአንተ እንዲገለጥ

ትዕቢት ምቀኝነት ላንተ አይጠቅምህም
ወደ ጌታ ደጅ ሊያደርስህ አይችልም
ይልቅስ ተዘጋጅ ስንቅህንም ሰንቅ
የእግዜርን ጥሪ ንቁ ሆነህ ጠብቅ

እንዳትደናገጥ ወንዙ ቢሞላብህ
መንገድህን ቀጥል በእምነት በርትተህ
ትጎናፀፍ ዘንድ የድል አክሊልን
ተከተል ጌታህን በመተው ሁሉንም

አንዲበዛልህ ሰማይ ያለው መዝገብ
በምድር ላይ ሳለህ ከኣሁኑ ሰብስብ
ያልዘራኸውን ማጨድ አትችልምና
ከአሁኑ ታገል ጊዜ አለህና

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top