አዝ. ስላንተማ ብዙ ምናገረው አለኝ /2/
የትኛውን አንስቼ የትኛውን እተዋለሁ
ጌታዬ ሥራህ እኮ ከአእምሮዬ በላይ ነው
1. እግ/ር ሃያል ነህ ማንም አትንቅም
ደካማን በመጣል አንተ አትታወቅም
ከጥንት የሰማነው በአይናችን ያየነው
ጻድቅነትህን እና ሰውን መውደድህን ነው /2/
አዝ. ስላንተማ ብዙ ምናገረው አለኝ /2/
የትኛውን አንስቼ የትኛውን እተዋለሁ
ጌታዬ ሥራህ እኮ ከአእምሮዬ በላይ ነው
2. ጥንት አባቶቻችን ሥራህን አወሩ
ድንቅ ታምራትህን እየመሰከሩ
ሥራህ እግ/ር ሆይ ከአእምሮ በላይ ነው
እኔ ምስክር ነኝ በአይኔ አይቻለሁ /2/
አዝ. ስላንተማ ብዙ ምናገረው አለኝ /2/
የትኛውን አንስቼ የትኛውን እተዋለሁ
ጌታዬ ሥራህ እኮ ከአእምሮዬ በላይ ነው
3. የማወራው አለኝ የምመሰክረው
ስላንተ ምህረት ፍቅር የምናገረው
ስለሰው ልጅ ሃጢያት ልጅህን ሰጥተሃል
በእውነተኛ ፍቅርህ እኛን አድነሃል /2/
ከአእምሮ በላይ ነው ፍቅርህ
እኛን መውደድህ /4/
ክበር እንጂ ሌላማ ምን እንላለን
በላይ በላይ ምስጋናን እንጨምራለን
በላይ በላይ ክብርን እንጨምራለን
ንገስ እንጂ ሌላማ ምን እንላለን
በላይ በላይ ምስጋናን እንጨምራለን
በላይ በላይ ዝማሬን እንጨምራለን /2/
ልነሳና ልነሳና ላክብርህ
ምክንያት አለኝ ብዙ ብዙ
ምክንያት አለኝ ክበር /3/
ምስጋና ላንተ ነው ክብርም ላንተ ነው
አምልኮ ላንተ ነው ስግደትም ላንት ነው
ያረክልን ብዙ ነው ጌታ /2/
ያረክልን ብዙ ነው አሃሃሃ /2/
ውዳሴ ላንተ ነው ቅዳሴ ላንተ ነው
ጭብጨባ ላንተ ነው እልልታ ላንተ ነው
ያረክልን ብዙ ነው ጌታ /2/
ያረክልን ብዙ ነው አሃሃሃ /2/
