ቃል ኪዳኔ ነህ የመጨረሻ
ያላንተ ጌታ ሌላም አልሻ
ትርጉም ሰጥቶኛል ዛሬ ኑሮዬ
ሥለሆንክልኝ ሁሉም ነገሬ
ለነፍሴ ትርጉም ሰጠሃት ፍቅር
ኣንተን ስታገኝ ኖረች በክብር
ተስፋ ስላላት ከአንተ ዘንድ ጌታ
ፍፁም አትሰጋም የነገን ፈርታ
አሃ አሃ ኣንተ ህይወቴ
የኑሮዬ ጣዕም
ዛሬ ገብቶኛል
የመኖር ትርጉሙ
አይለመድም ካንተ ወጭማ
ፍቅርህ ልዩ ነው እጅግ ሚስማማ
ወረት ኣያውቀው ጊዜ አይለውጠው
የአንተ መውደድህ ሁል ጊዜ ያው ነው
አንተ ፊተኛ ኣንተ ኋልኛ
አምላኬ ለእኔ እስከ ወዲያኛ
ቃል እገባለሁ ላላመልክ ሌላ
የእምነት ማሰሪያዬ ቃል ነውና
