ወዶናል አዳነን

114

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት
እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ
እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ
እግዚአብሄር አለሙን እንዲሁ ወዷል
ወዶናል አዳነን/4/ ወደደን አዳነን /4/

ማንም አልነበረም ለዚህ የተገባ /2/
ምን አይነት ፍቅር ነው ልጅህ ሞት ሲገባ አንተ ለኛ ባባህ
እውነተኛ አረከው የህይወት መንገድ ወዳንተ መንገድ
ብቸኛ መዳኛ በቅንም የሚፈረድ የሚፈረድ

በእምነት የሚገኝ በደሙ የሆነ በጸጋው የሆነ
በእግዚአብሄር ጽድቅ አለው በኢየሱስ ላመነ ላመነ

ለአይሁድም አርሱ ነው ደግሞም ለግሪክ ሰው በምድር ላለ ሰው
የዘላለም ህይወት በሩ ኢየሱስ ነው ቃሉ እንዳለው

አኛም በእርሱ ሆነን የእግዚአብሄር ጽድቅ በነፍስ ልንጸድቅ
ኀጥያት ባላወቀው በኢየሱስ እርቅ ሆነ መታረቅ
ከሁለት ተቀዲል የሀጢአት መጋረጃ ሽፋን መጋረጃ
መንገዱ ክፍት ሆኗል ወደ አብ መሄጃ /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top