አቤት ያንተ ስራህ ያስገርማል
ቅንና ልክ ስህተትን መች ያውቃል
ሚዛንህን ማንም አይሰብረውም
መልካም ብቻ ክፋት አያውቀውም /2/
1. ምንም በሌለበት በደረቁ ምድር
መናን አውርደህ ህዝብህን የምትመግብ
የኃጢአንን ምኞት ትገለብጣለህ
የጻድቃንን ነፍስ እንተ ታጠግባለህ /2/
ነፍሳት ሁሉ እግዚአብሔርን ባርኩ
ምስጋናውን ሁሉ በማደሪያው አብዙ
ፍጥረታት በሙሉ ስሙን አወድሱ
ልዩ ነውና የጌታ አሰራሩ
2. በማዕበል ውስጥ ሆነን እጅግ በሚያስፈራ
ቃልህን አውጥተህ ንፋሱን ምትመራ
ለተጨነቀች ነፍስ መፍትሄ ትሰጣለህ
ሁሉንም ገስጸህ ሰላም ትሞላለህ /2/
ነፍሳት ሁሉ ………..
አቤት ያንተ……………
3. በሰይፍና በጦር የሚያድን አይደለም
የእስራኤል አምላክን የሚመስል የለም
ታምራቱን አየ አህዛብ በሙሉ
በጠጠር ወደቀ ጀግና የተባለዉ
ስራው ፍጹም – የኛ ጌታ
እንደ ቃሉ – ታማኝ ነውና
የእውነት አምላክ – ይመልሳል
ለታመኑት – ቶሎ ይደርሳል
4. አምላኩን ያመነ ምንስ ያሰጋዋል
የአንበሶችን አፍ ዘግቶ ይጠብቀዋል
መልካም መንፈስ ያለው ጌታው ያከብረዋል
ፍርድ እንኳን ቢቀበል ሞገስ ይሆነዋል
ስራው ፍጹም – የኛ ጌታ
እንደ ቃሉ – ታማኝ ነውና
የእውነት አምላክ – ይመልሳል
ለታመኑት – ቶሎ ይደርሳል
ወ፡ እንወራረዳለን ስራህን ከሚንቁ
ታምራትህን አይተው ላንተ ይመሰክራሉ
ሴ፡ እንወራረዳለን ብዙ አውቀናል ከሚሉ
የጥበብህን ጫፍ እንዳልነኩት ያውቃሉ
ወ፡ እንወራረዳለን በስልጣን ከተመኩ
ጊዜ ማይሸረውን ዙፋንህን ያያሉ
ሴ፡ እንወራረዳለን ሊተካኩህ ከሚሹ
ያንተን ሃያልነት ከብርህን ይረዳሉ /2/
