የሰማይ ፃድቆች
የእግዚአብሔር ወዳጆች
በትእግስታቸው
በመንግስት ወረሳቸው
ብትታዘዙለት
ለፈጣሪያችሁ
የአለምን ሁከት
ድል አደረጋችሁ
ቅዱሳን መላእክት
በሰማይ ያላችሁ
የአምላካችሁ ፊት
ዘወትር ታያላችሁ
ለፃድቃኑ ጌታ
ሲሰጣቸው ቦታ
ምን ያህል ደስታ
እንዴት ያለ እልልታ
ስጋዊ ፍትወት
በምድር ያገናኛችሁ
አሁን በሰማያት
እንዴት ደስ ይላችሁ
ስለመልካም ነገር
ሁሉንም ትተው
ባረካቸው እግዜር
ደሞዝ ሰጣቸው
