የጽዮን ልጅ ደስ ይበልሽ
ድለኛው ጌታ ከአንቺ ነውና
ተነሽ ፈክተሽ ብርሐን መጥቶልሻል
የያህዌ ክብር በአንቺ ታይቷል
ጨለማው ምድር ተሸፍኗል
ህዝቡ ጥላው ስር ተረቷል
ነቅተሽ እስቲ ተመልከቺ
ጉዞው ሆኗልና ወዳንቺ
ልጆች ከሩቅ መጥተዋል
ክንዶችሽም ላይ አርፈዋል
ታይዋለሽ ትደነቂያለሽ
ከልብ ትፈነድቂያለሽ
መጥቷል ሀብት ሁሉ
ወደአንቺ ከህዝብ ሁሉ
እንደእርግብ ወደጎጆዋ
የተርሴስ መርከብ ሆኖ መሪዋ
እንደደመና የሚጓዙት
ወደአንቺ ነው የሚሰበሰቡት
ተረስተሽ የነበርሽው
ተጥለሽ የተናቅሽው
ዘወትር ተሆኛለሽ ኩራቴ
በአንቺ ሆኗል መደሰቴ
ፀሐይ አይበራልሽ
ጨረቃም አትወጣልሽ
ግን ያህዌ ይሁን ብርሐንሽ
አምላክሽና ውበትሽ
ፀሐይም አይጥለቅብሽ
ጨረቃም አይጥፋብሽ
ያህዌህ ይምጣልሽ በይፋ
