ይሻላል ህይወት

274

ይሻላል ህይወት ኢየሱሴ ያለበት /2/
ሰላም ነው ህይወት የኔ ጌታ ያለበት /2/

ከውሀ የወጣ አሳ መኖር እንደማይችለው
ሰውም ያለ ኢየሱስ ህይወቱ እንዲሁ ነው

ታዲያ እስኪ ምንድነው ወንድሜ የምትጠብቀው
ፍጠን ጊዜው አሁን ነው ራስህን ለጌታ ስጠው
ታዲያ እስኪ ምንድነው እህቴ የምትጠብቂው
ፍጠኚ ጊዜው አሁን ነው ራስሽን ለጌታ ስጪው

የአይምሮ ሰላም የልቦና ደስታ
ምንጩ እርሱ ጋ ነው ለፈለገው ጌታ
ታድያ ወዴት ወዴት አማራጭ ፍለጋ
መፍትሄው ኢየሱስ ነው ወደ እርሱ ተጠጋ

እውነት የመሰለህ የሀሰት ድለላ
ዙርያህን ከቦሀል እንዳትሆን ተላላ
የጥበብ መጀመርያ የፍጥረታት መሪ
አድርገው የራስህ የህይወትህ መሪ

አንድ ነው መንገዱ ሁለተኛ የለም
በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት የዘልአለም
ቢመስላትም አለም ይህ ህይወት ሞኝነት
ለሚያምን ጥበብ ነው ማስተዋል ያለበት

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top