በዛ ምህረትህ

-

በዛ ምህረትህ /2x ጌታ ተመስገን
አሜን ተወደስ በዛ ምህረትህ

1.ደዌ ከፍቶብኝ ልሞት ሳጣጥር
መድሀኒት አጣሁ በሽታን ሚሽር
አለሁ እያልከኝ ደርሰህ ከጎኔ
ተመስገን እየሱስ ቋሚ መድህኔ

በዛ ምህረትህ /2x ጌታ ተመስገን
አሜን ተወደስ በዛ ምህረትህ

2.ጉድፍ ተብዬ የተረሳሁኝ
እንደሞተ ሰው የተቆጠርኩኝ
ዛሬ ግን ጌታ ከትቢያ አነሳኝ
አለኝታዬ ነው ይባረክልኝ

በዛ ምህረትህ /2x ጌታ ተመስገን
አሜን ተወደስ በዛ ምህረትህ

3.አይኖቼን ዳስሶ ብርሀን ያሳየኝ
ገላዬን አየቶ ፈፅሞ አነፃኝ
ተመለክ ጌታ ዛሬም ተወደስ
ክበር እየሱስ ኤልሻዳይ ንጉስ

በዛ ምህረትህ /2x ጌታ ተመስገን
አሜን ተወደስ በዛ ምህረትህ

4.ሆኜ ቢያየኝ መጥፎ ሀጢያተኛ
ቅን አይታየኝ ለሰው አልተኛ
ተመለስ ልጄ ብሎ ገሰጸኝ
ይመስገን ጌታ ከእሳት ያወጣኝ

በዛ ምህረትህ /2x ጌታ ተመስገን
አሜን ተወደስ በዛ ምህረትህ

5.ምህረቱ እንደእኔ የበዛላችሁ
ስራው ዘወትር ያስደሰታችሁ
ተመስገን በሉት አትስጡት ፋታ
አንግሱት እሱን ሁሌ በእልልታ

በዛ ምህረትህ /2x ጌታ ተመስገን
አሜን ተወደስ በዛ ምህረትህ

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top