በሃይልህ ደግፈን

30

የቅዱስ ቤ/ክ ፅናቷ የሆንከው
መንፈስ ቅዱስ ጌታ ተሰብስበን አለን
በሀይልህ ደግፈን እንዳንበታተን
እግዚአብሔር ልጆችህ መሆን እንሻለን /2/

ትዛዝህን አፍርሰን በከንቱ ስንኖር
በሐጥያታችን አንተን ስናሳዝን ነበር
ከጥፋት ጉዞአችን ከስህተት መልሰን

በቤትህ አኑረን ንፁህ ልብን ሰጥተህ ፈጥረህ

ከዛሬ ጀምሮ እኛ አንታወክም
ተጐሳቁለን ስታይ አልፈኸን አታውቅም
ዛሬም እንደጥንቱ በአንተ እንድንኖር
ቅዱስ መንፈስህ በውስጣችን ይኑር /በልባችን ይኑር/

ከቀኝ ከግራም ፈተና ቢከብም
ማእበል ቢነሳም እጅጉን ቢያይልም
ከእንግዲህ አልሰጋም ምን እንሆንና
ሁሉን ዝም የሚያሰኝ ኢየሱስ አለና /በረዳቴ አለና/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top