አይኖቼ ተከፍተው አንተን ይመልከቱ
እንዳልሰናከል ጠፍቶብኝ መንገዱ
አንተ መንገዴ ህይወቴ
ብርሃን ያየሁብህ ለእኔ ነፃነቴ
የአለም ውስጥ ዝና ዙሪያዬን ቢከበው
እንዳያታልለኝ እጄን በእጅህ ያዘው
ዘመኔ እንዳይሆን የከንቱ የዋዛ
ልቤ በአንተ ታምኖ ለክብርህ ይገዛ
ይሁን ጉብዝናዬ ኣንተን ማከብርበት
ከሁሉ አስበልጬ ላንተ ምኖርበት
በፀጋሀ ኣግዘኝ ብርታት ሁነኝና
ዛሬ ካለኝ ይልቅ ቅባትህ ይብዛና
ሁንልኝ እርካታ ለህይወት ዘመኔ
አንተን መርጫለሁ እንድትሆን ኑሮዬ
ግራ ቀኝ ኣላይም አማራጭ ፍለጋ
አንተን አግኝቻለሁ ልቤ ብሏል ረጋ
