ልመናዬን ስለሰማ

42

ልመናዬን ስለሰማው ጌታን ልባርከው
አሠራሩ ቢዘገይም ለካ ለበጎ ነው /2/

እንደርሱ ያለ የለም እንደርሱ ያለ /2/
ሁሉን አዋቂ እስኪ ማነው እንደርሱ ያለ
እግዚአብሔር ብቻ ሁሉን ቻይ በዙፋን አለ

1. አቅሜን ጨርሶ መፍትሔ ያጣሁበት
በነጋ በጠባ እንባ ያፈሰስኩበት
ለካስ አባት አለኝ የሚያየኝ ከላይ
ፀሎቴ ሰመረ ተከፈተ ሰማይ

ሰመረና ስለቴ አንደበቴ ተፈታ
ሰመረና ፀሎቴ ወግ አየሁ በጌታ
ሰመረና ስለቴ እኖራለሁ በደስታ
ሰመረና ፀሎቴ አፌን ሞላው በእልልታ

ልመናዬን ስለሰማው ጌታን ልባርከው
አሠራሩ ቢዘገይም ለካ ለበጎ ነው /2/

እንደርሱ ያለ የለም እንደርሱ ያለ /2/
ሁሉን አዋቂ እስኪ ማነው እንደርሱ ያለ
እግዚአብሔር ብቻ ሁሉን ቻይ በዙፋን አለ

2. መስሎኝ ነበረ እኔስ የተረሳሁ ከቶ
ከልቤ ደረስ ዘግይቶ ተነስቶ
አይንን የፈጠረ እንዴት ሳያይ ያልፋል
ጆሮን የፈጠረ እንዴት እርሱ አይሰማም

ሰመረና ስለቴ አንደበቴ ተፈታ
ሰመረና ፀሎቴ ወግ አየሁ በጌታ
ሰመረና ስለቴ እኖራለሁ በደስታ
ሰመረና ፀሎቴ አፌን ሞላው በእልልታ

ልመናዬን ስለሰማው ጌታን ልባርከው
አሠራሩ ቢዘገይም ለካ ለበጎ ነው /2/

እንደርሱ ያለ የለም እንደርሱ ያለ /2/
ሁሉን አዋቂ እስኪ ማነው እንደርሱ ያለ
እግዚአብሔር ብቻ ሁሉን ቻይ በዙፋን አለ

3. አውቀዋለሁ ክንዱን የለም የሚሳነው
አምናለሁ ይችላል ችግሬን ሊሽረው
ከቶም አላፈርኩም አየሁታ ችሎ
ኮራሁኝ ባአምላኬ ሁሉን አስተካክሎ

ሰመረና ስለቴ አንደበቴ ተፈታ
ሰመረና ፀሎቴ ወግ አየሁ በጌታ
ሰመረና ስለቴ እኖራለሁ በደስታ
ሰመረና ፀሎቴ አፌን ሞላው በእልልታ

ልመናዬን ስለሰማው ጌታን ልባርከው
አሠራሩ ቢዘገይም ለካ ለበጎ ነው /2/

እንደርሱ ያለ የለም እንደርሱ ያለ /2/
ሁሉን አዋቂ እስኪ ማነው እንደርሱ ያለ
እግዚአብሔር ብቻ ሁሉን ቻይ በዙፋን አለ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top