በትህትና ተሞልታ እ/ር ያለውን ተቀብላ
የማዳኑ ሚስጥር ተፈፀመ
የአዳም ዘር በሙሉ በእርሱ ዳነ
ቅድስት ናት የኢየሱስ እናት
ብፅዕት ናት የጌታዬ እናት /2/
1. የአዳም ዘር በሙሉ በሃጥያቱ
ይጠባበቅ ነበር የነፍስ ሞቱን
ታዛዥና ትሁት የሆነችው
አዳኙን ኢየሱስ ወለደችው
በትህትና ተሞልታ እ/ር ያለውን ተቀብላ
የማዳኑ ሚስጥር ተፈፀመ
የአዳም ዘር በሙሉ በእርሱ ዳነ
ቅድስት ናት የኢየሱስ እናት
ብፅዕት ናት የጌታዬ እናት /2/
2. ለእ/ር እጅግ የተመቸች
ከናዝሬት ከተማ የተገኘች
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት
የኢየሱስ እናት ማርያም ናት
በትህትና ተሞልታ እ/ር ያለውን ተቀብላ
የማዳኑ ሚስጥር ተፈፀመ
የአዳም ዘር በሙሉ በእርሱ ዳነ
ቅድስት ናት የኢየሱስ እናት
ብፅዕት ናት የጌታዬ እናት /2/
