በአዲስ ዘመን አዲስ ነገር
የእግዚአብሔር ስም እንዲከበር
እንጠብቃለን በናፍቆት
ያደርገዋል ምን ተስኖት
1. የተዘጋው ደጅ ተከፍቶ
የታሰረው ነፃ ወጥቶ
እንሰማለን የድል ዜና
እንዘጋጅ ለምሥጋና
በአዲስ ዘመን አዲስ ነገር
የእግዚአብሔር ስም እንዲከበር
እንጠብቃለን በናፍቆት
ያደርገዋል ምን ተስኖት
2. በፍፃሜ ሞት አይሆንም
ትንሣኤ አለ ለሙታንም
ያለቀስነውን እምባ ሊያብስ
ከተፍ ይላል ጌታ ኢየሱስ
በአዲስ ዘመን አዲስ ነገር
የእግዚአብሔር ስም እንዲከበር
እንጠብቃለን በናፍቆት
ያደርገዋል ምን ተስኖት
3. ብቸኛ ሴት በእንባ ያለች
መካኒቱ ትወልዳለች
የሣራ አምላክ የራሔልም
ጥቃት አይቶ ዝም አይልም
በአዲስ ዘመን አዲስ ነገር
የእግዚአብሔር ስም እንዲከበር
እንጠብቃለን በናፍቆት
ያደርገዋል ምን ተስኖት
4. ሰማያዊ በላአደራ
የወንጌል ዘር በእምነት ይዝራ
የበቀለው ሳይጨነግፍ
ይሰበስባል ብዙ እጥፍ
በአዲስ ዘመን አዲስ ነገር
የእግዚአብሔር ስም እንዲከበር
እንጠብቃለን በናፍቆት
ያደርገዋል ምን ተስኖት
5. ውሃ ያጣ አሣ መሣይ
ወንዝ የሌለው ደረቅ ሚታይ
ጌታ ይስጠው ረጅም ዕድሜ
ለሱም ያያል ልምላሜ
በአዲስ ዘመን አዲስ ነገር
የእግዚአብሔር ስም እንዲከበር
እንጠብቃለን በናፍቆት
ያደርገዋል ምን ተስኖት
