በደምህ ያሸነፍክ ኃጢያቴን በሙሉ
መድኃኒዓለም ነህ መድኃኒት የሁሉ
ለኛ ምትሰዋ በቅዱስ ቁርባን
መድኃኒዓለም ነህ ስምህ ይመስገን
ስምህ ይመስገን ሃያሉ እግዚአብሔር
ስለውለታህ ይድረስህ ክብር
ስምህ ይባረክ የኢየሱስ አባት
መድኃኒት ልከህ ሰጠኸን ሕይወት
እኛ ከምንሞት አንተ ለመሞት
ለኛ ለሰዎች ልትሆን መስዋዕት
በመስቀል ላይ ራስህን ሰጠህ
በፍቅር ላይ ዓለምን አየህ
ራስ አሳልፎ ለሰው ከመስጠት
የበለጠ ፍቅር የለም በእውነት
አንተ ግን ጌታ ይህን አደረግህ
እኛን ልታድን መሞትን መረጥህ
ከራስ አብልጠህ ስለምትወደን
ወዳጅ እንዳጣ ልጅ ስለማተወን
በነገር ሁሉ ከፍ ከፍ በል
አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የሆንከው ልኡል
