1. ያለህበት ቦታ ለካ ቅዱስ ነበር
ደፍሬ ቀረብኩት የማየውን ተአምር
በፊትህ የመቆም ሳይሆን ለአንተ ክብር
ምሥጢሩን ዘንግቼ ርቆኝ ሆኖ ስውር
ጫማዬን አወለቅሁ ማምለኬን ልጀምር /ዘፀ 3፡15/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
2. ለመቆም በፊትህ ዕድሉ ተሰጥቶኝ
ግርማህን እንዳደንቅ ውበትህ መስጦኝ
ዘንግህን ዘርግተህ ሞገስህ እየጠራኝ
ምንኛ ክብር ነው አንተን እንዲህ መቅረብ
ስጦታህ ነው እንጂ ነጻ አድርገህ የምትስብ /አስቴር 5፡2/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
3. በጌታ ፊት የሚቆም ማንነትን ይዘህ
መጠሪያህ አድርገህ ገብርኤል ነኝ ብለህ
ብስራትን ለመስጠት ቀና ልዑክ ሆነህ
በመንፈስ አንድ ሆነህ የላከህን መስለህ
የእርሱን ክብር ገለጽክ ደኀንነትን አውጀህ /ሉቃ 1/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
4. የማልጠብቀውን ልዩ ትኩረት ሰጥተህ
በስሜ ጠራኸኝ ከዛፍ ውረድ ብለህ
ጸያፍ ሆኖ ሳይታይ ምኔም ሳይቀርህ
መቆሜ በፊትህ ሲያበቃኝ ለክብርህ
ልቤን ክፍት አደረከው ለጋስና ርኀሩኀ /ሉቃ 19/
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
5. በቤትህ ፊት መቆም ሁሌ የምመኘው
ልብን የሚማርክ ውስጥን ሚያረካው
ነጻ ወይ እስረኛ ለይቼ ሳላውቀው
ምክንያት የሚያነሳሳ ይኼ ነው የምለው
መለየት አስችለኝ መንፈስ የሞላውን
አዝ. ከፊትህ ከቤት ብርሃንህ ከሞላው
ማንነቴ በአንተ ተሠይሞ እስከማየው
ለክብርህ አቁመኝ እና እኔም እቆማለሁ
ምንም ሳይገድበኝ ነጻ ሆኜ ሳለሁ
