አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
1. ስንቱ ተወርቶ ስንቱ ይተዋል ጌታ ሆይ
ለእኔ ያረከው ቀና ብዬ አንተን ሳይ
ከጭንቀት አውጥተህ ሰላም የሰጠኸኝ አባት ሆይ
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን የሱስ ሆይ
አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
2. መሬት በሙሉ ወደ ወረቀት ቢለወጥ
ባህር በሙሉ ወደ ቀለምም ቢቀየር
ያረከው ጌታ ቢታይ የአንተ ውለታ
በፍጹም አልችልም ቃላት ያጥረኛል ጌታ
አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
3. ቢጻፍ አያልቅም ጌታ የአንተ ውለታ
ስራህ ድንቅ ነው ከቶ የማትረታ
የእስራኤል አምላክ ከቶ የማታንቀላፋ
የእስራኤል አምላክ ከቶ የማታንቀላፋ
አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
