በፍቅርህም ማረከኝ /ጌታ/ /2/
በጉያህ አቀፍከኝ ኢየሱስ
በቤትህ ሰብሰበከኝ
ለእኔ የሚሻለውን አንተ ታውቃለህ
ለበጐ ማድረግ ሁሉን ትችላለህ
ለኔ የሰጠኸኝን ፀጋህን አብዛህልኝ
የህይወቴ ጌታ መንገድህን ምራኝ
እውነተኛ እረፍቴ ጌታዬ አንተነህ
አባቴ ሁሉንም ማድረግን ታውቃለህ
ቸሩ ኢየሱስ ሆይ ብርሐንን አብራልኝ
የልቤን ጨለማ ከእኔ አርቅልኝ
ኢየሱስ ፊትህን ከእኔ አትመልስብኝ
ታምኛለሁና እንዳላፍር አድርገኝ
መፀፀቴን አይተህ ሃጥያቴን አንጻልኝ
የመንፈስ ጭንቀቴን አንተ አቃልልኝ
ከምኞቴ እስራት እንድፈታ አግዘኝ
የፍቅርህ ነፀብራቅ እንድሆን አድርገኝ
ከውስጤ ፍላጐት በአንተ እረፍት ስጠኝ
በልቤ ሰላምን እንዳገኝ አድርገኝ
