ቤተልሔም

1

ቤተልሔም ዛሬ ሌሊት
ተከባለች በታምራት
አምላክ ወሰብ ተወልዶላት
ተከባለች በመላእክት
ክበር ይሁን በሰማይ በምድር

የእስራኤል ንጉስ የዳዊት
ተወልዷል በዚች ሌሊት
የገብርኤልም ብስራት
ተፈፀመ ዛሬ በእውነት
ክበር ይሁን በስማይ በምድ

እረኞች ሆይ ንገሩን
የዛሬን በዓል ክብሩን
ብንሰማ ዜማችሁን
መጣን እኛም ደስ ብሎን
ክበር ይሁን በሰማይ በምድር

የአዳም ልጆች ነቃ በሉ
የመልአኩን ቃል ተቀበሉ
ሰላማችን መጣ እልልበሉ
ሊያድነን ነው ከሐጥያት ሁሉ
ክበር ይሁን በሰማይ በምድር

ኢየሱስ ሆይ የዳዊት ልጅ
ሰውረን ከዲያቢሎስ እጅ
ክፈትልን የሰማይን ደጅ
አውጣን ስበህ ከሲኦል ደጅ
ክበር ይሁን በሰማይ በምድር

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top