አንዳች ሌላ የለኝ ምሰጠህ
ጌታ ለዋልክልኝ ለክብርህ
ምስጋና ግን አለኝ እሰዋለሁ
ይህ ግን ለእኔ ልማዴ ነው
በገባሁ በወጣሁበት
ያንተ ስም በሚጠራበት
አንድ ሆኜ ተመስገን እላለሁ
በዚህ ነው ልቤ እፎይ ሚለው
ተመስገን /3/ አምላኬ ተመስገን
ተመስገን /3/ የሱሴ ተመስገን
ተባረክ ተወደስ
ድምፄ ከዙፋንህ ከማደሪያህ ይድረስህ
ተባረክ ተወደስ
ከፍ በል አምላኬ መንግሥትህ ይቀደስ
መዝሙሬን በቃላት መንዝሬ
የውስጤን እንዲህም ዘምሬ
መች በቃኝ መቼ ተቀምጬ
አይደርቅም የምስጋና ምንጩ
እየበዛ ላለው ባርኮት
ደግሞ ስላኖርከኝ በሕይወት
ሊሆን ስላሰብክልኝ ጌታ
ስለሆሉም ያንተ ውለታ
