እንዳንተ ያለ የለም

99

አዎ /2/ እንዳንተ ያለ የለም በሰማይ
በሕያዋን መካከል በምድር ላይ /2/
አንተ በእውነት ታላቅ ነህ
አንተ በእርግጥ ታላቅ ነህ
እንዳንተ የሚሆን እስኪ ማን አለ /2/

ለድሃ መበለት ጠያቂ ለሌላት አሃሃ
ሰው ገና በሩቁ /2/ ለሸሻት ኦሆሆ
ጊዜያትን ቆጥረህ ለሷም ትደርሳለህ አሃሃ
ዕንባዋን ከዓይኗ ታብስላታለህ
ጌታ ተባረክልኝ
የሱስ ተባረክልኝ
ሌላማ የምልህ የለኝ /2/
አንዳንተ እኔስ አላየሁኝ

ታች ወርዶ ላይ ወጥቶ ሰው ፊት ለነሳበት አሃሃ
ተስፋው ከኑሮው ላይ ለተሟጠጠበት አሆሆ
ባፈረበት ምድር ምርኮን ታወርሳለህ
ዘመኑን የጥጋብ ታደርግለታለህ

ጌታ እንዳንተ ማን አለ
እስኪ እንዳንተ ማን አለ /2/
ይህን ሊያደርገው የቻለ
አዎ….

ጥበብህ አይለካ ኃይልህ አይፈተን አሃሃ
ሁልጊዜ ብርቱ ነህ በየትኛውም ዘመን አሆሆ
የምድሩን ትቶ ሰው አንተን ቢጠጋ

በዝቶለት ይኖራል በፀጋ ላይ ፀጋ
አንተ ከማንም በላይ ነህ
ጌታ ከምንም በላይ ነህ
አምሳያም እኩያም የሌለህ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top