- አድርገህልኛል /ብዙ/2x በህይወቴ
ድንቅን ሆኖልኛል ባንተ መዳኒቴ
ባይመጥንህ እንኳን ለሰጠኸኝ ፍቅር
ከልቤ የሆነ ምስጋና ላብዛልህ
ተመስገን /2x/
ዛሬን ያየሁት ባንተ ነዉ
የማያልቀዉ ምህረት በዝቶልኝ ነዉ
የቃላቴም ብዛት አንተን ባይገልፅልኝ
ደጋግሜ ልበልህ ተመስገንልኝ
2. አምላኬ ፍቅርህ እጅግ ሚደንቀኝ
ነፍስህን አሳልፈህ ለኔ የሰጠኸኝ
ፍቅር ነህ አንተ እዉነተኛ ፍቅር
ምስጋናዬን ልስጥህ ለክብርህ ልዘምር
ልዘምር ከፍ ላድርግህ
ባንደበቴ ካለዉ ዉስጤ ከሞላኸዉ
የተትረፈረፈዉን ምስጋናዬን ይኸዉ
3. በሀጥያቴም ብወድቅ አንተን ባሳዝንም
ለሞት አትተወኝ ጥለኸኝ አትሔድም
በምህረት እጆችህ እኔን ታነሳለህ
የፍቅር አምላክ ጌታ መልካም ነህ
መልካም ነህ እጅግ መልካም ነህ
የምህረት አምላክ ነህ አንተ የኔ ጌታ
የማትለዋወጥ ጠዋትም ማታ
