ተሸንፌያለሁ በትልቁ ፍቅርህ
ህይወት አግኝቻለሁ በማዳንህ
ከእንግዲህ አልጠፋም ከቤትህ
ዘወትር እገኛለሁ ከመቅደስህ
ከማደርያህ አይርቅም እግሬ
ስለሰበርከዉ የሀጥያት ቀንበሬ
ኢየሱስ ነህና ሁሉም ነገሬ
ከአንተ ስሆን ነዉ ሀይልና ክብሬ
ያሰብኩት መልካም ሁሉ እንዲሳካ
ልቤ በሀሴት ተሞልቶ እንዲረካ
ደጀ ሰላምህ እረግጣለሁ ሁሌም
ካንተ አይርቁም አካሌም መንፈሴም
መስዋዕቴን ላቅርብ ደጅህን መጥቼ
በምስጋና መዝሙር አፌን አዘምሬ
ተንበርክኬ ልደር ከእግርህ ስር ሆኜ
መላዉ እኔነቴን ላንተ አስገዝቼ
ዝናብ አያግደኝ ጎርፉንም አልፈራ
በበረታዉ ክንድህ ታምኛለሁና
ዘመኑ ቢጨልም ቢበዛ መከራ
ዘወትር እሻለሁኝ መሆን ካንተ ጋራ
