ያ ድቅድቅ ጨለማ በላዬ የነበረው
መፅናናቴን ወስዶ ልቤን ያቆሰለው
ተረሳ አለፈ ዛሬም አስገረመኝ
እግዚአብሔር ተመስገን እኔም ታሪክ ኖረኝ
ተመስገን /2/ ምን ልበልህ ታዲያ ከዚህ በቀር /2/
ታሪኬ ተዘግቷል ነበር ብዬ እኔማ
በጠላቴ ሰፈር ማዘኔ ሲሰማ
ታዲያ ያ ሁሉ አልፎ ደስታ ሲሆን ቤቴ
ዛሬም እንዲህ እላለሁ በመላ አካላቴ
ተመስገን /2/ ጌታ ሆይ ምን ልበልህ ታዲያ ከዚህ በቀር /4/
የማይቻል ሲሆን በሰዎች እይታ
ሁሉን አስተካክሉ አየሁት ይህ ጌታ
በነገሮቼ ላይ ውዴ እየገባ
ይታበስ ጀመረ ያነባሁት እንባ
ተመስገን /2/ ምን ልበልህ ታዲያ ከዚህ በቀር /2/
አምላኬ ያደረገልኝን ቆጥሬ አልዘልቀው
ተመስገን /3/ እለዋለው /2/
