አመሰግንሃለሁ

106

ካሁን በፊት ካሁን በኃላ
ካገኘኸው ከምታገኘው በላይ /2/
ምስጋናን ልስጥህ/ላብዛ በዛም ላይ

ምስጋናን / አምልኮን ልስጥህ
ይሁን ላንተ አምላኬ(2) ይኸው ላንተ አምላኬ
ስትረካ እረካለሁ በጥማቴ ልኬ
ይሁን /ይኸው ላንተ አምላኬ
ችዬ እንደው ባረካህ አልፌ ከልኬ

አስቤ /3/ ያረከውን ፊቴ ሰብስቤ
ጌታዬ ሆይ ተመስገን ብልህ /2/
ላረከው/አምላኬ ይህም አይመጥንህ
አውቃለሁ እንደማይመጥንህ

ቢሆንም ገና እቀኛለው
አልረካም ውስጤ ቃል አለው
ጠላቴ በቅቶኝ ሲመስለው /2/
እኔ መዘመሬን/ማመስገኔን አልተው

አመሰግንሃለሁ ግን ይሄ አይበቃም (3)
መንፈሴ በዚህ አይረጋም
ተመስገን እልሃለሁ ግን ልቤ አይረካም (3)
ያንስሃል ይሄ አይበቃም

ያንስሃል ጌታ ያንስሃል
ዝማሬ መች ይበቃሃል
ያንስሃል ጌታ ያንስሃል
ከዚህም በላይ ይገባሃል

ጎህ ቀደደ ደግሞ ልነሳ
የለሊቴን ግርማ ሳልረሳ /2/
አርፋለሁ እንጂ ይመስገን ብዬ
አልገልጸው የሆዴን ጠቅልዬ

እንዴት ላክብርህ ልገዛ
በወደድከው መንገድ ልሰማራ
ከዚያማ እረካለሁ ስስማ
እንደልብህ ሆኖ ይህ ዜማ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top