ተሰምቷል ጸሎቴ

266

ተሰምቷል ጸሎቴ አብቅቷል ጩኸቴ
ከልቤ ለምኜው ጌታን እንቆቅልሾቼን ፈታ
ከልብ የሚራራ ለልጁ ደርሳልኝ አይሁኝ እጁ

ታማኝ ሆኜ እያለሁ ተገዢ ለቃሉ
የሚደሰትብኝ ሆኜ አገልጋዩ
ግን በፍጹም አጣሁ ዘሬን የሚተካ
አንዳች አላገኘሁ ከቶ የሚያረካ
መዘግየቱ ጌታ ለጊዜው ነው ለካ
ይስሀቅን ሰጥቶኛል ልቤ በእሱ ረካ

ማየት ከቶ አልችልም ብርሀን ኣላውቅም
ታሪኬ ሊቀየር ተስፋ ባይኖረኝም

የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲያልፍ ባጠገቤ
እርዳኝ ብዬ ጮህኩኝ ለመንኩት ከልቤ
ምን ትፈልጋለህ ብሎ ጠየቀኝ
በደስታ ተሞላሁ ማየት አስችሎኝ

ሩህሩህ መልካም አምላክ እውነተኛ ዳኛ
በሀጢአት ላደፈ የሚሆን መጽናኛ
በማያልቅ ምህረቱ መማር ማይታክተው
ልመናን በጊዜው መልሶ ሚያኮራው
ለምኜው አገኘሁ ጸሎቴ ተሰምቶ
ለምስጋና ቆምኩኝ ልቤን ደስታ ሞልቶ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top