የደስታ መዝሙር እንዘምር

267

የደስታ መዝሙር እንዘምር
ስራውንም ሁሉ እንናገር
ላረገልን መልካም ነገር
ስሙ ይክበር እግዚአብሔር /2/

1. እግዚአብሔርን እናመስግን ባዲስ ቅኔ እንዘምር
ባማረ ዜማ በደስታ አምላካችንን እናክብር
ላደረገልን ውለታ እንደገና ምስጋና
ለእግዚአብሔር ይሁንለት አምላካችን ነውና

እናመስግነው አዎ ይመስገን
እግዚአብሔር ስሙ ይክበር /2/

የደስታ መዝሙር እንዘምር
ስራውንም ሁሉ እንናገር
ላረገልን መልካም ነገር
ስሙ ይክበር እግዚአብሔር /2/

2. ቸርነትና ምህረቱን ፍቅሩን ላበዛልን
በሽብሸባ በእልልታ እግዚአብሔርን እናመስግን
ጌታ የዋለልን ውለታ አይቆጠር አይነገር
መልካም ነውና አባታችን ለስሙ ሁሌ እንዘምር

ሀሌሉያ አዎ እንዘምር
እግዚአብሔር ስሙ ይክበር /2/

የደስታ መዝሙር እንዘምር
ስራውንም ሁሉ እንናገር
ላረገልን መልካም ነገር
ስሙ ይክበር እግዚአብሔር /2/

3. ውለታው ያለባችሁ ተነሱና ዘምሩ
ያደረገላችሁንም ከእኛ ጋራ አመስግኑ
እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይክበር በምስጋና
ለውለታው ምላሻችን ምስጋና ነውና

እናመስግነው አዎ ይመስገን
እግዚአብሔር ስሙ ይክበር
ሀሌሉያ አዎ እንዘምር
እግዚአብሔር ስሙ ይክበር

የደስታ መዝሙር እንዘምር
ስራውንም ሁሉ እንናገር
ላረገልን መልካም ነገር
ስሙ ይክበር እግዚአብሔር /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top