ቸር አፍቃሪን ጌታ ይዘን
በሆነው ባልሆነው ማቅ ነስንሰን እናዝናለን
ልጄ አልጥልህም አልተውህም ብሎ በራሱ ምሎልኝ
ለጊዜው ፈተና ቢከብደን
እንፅና እንበርታእንዳንወድቅ እጅ ሰጥተን
አምላካችን ማንን አሳፍሮ አየን ሰዎች እንታመን
ተስፋ የሰጠን /በተስፋ የሞላን አምላክ
የታመነ ነውና የተባረከ ነውና
በመጠበቂያችን ላይ እንጠብቀው እንበርታና
ቃሉን ያከብራልና
በሞኝነት ያለን ቢመስለን
እንጠብቀው ጌታን እንገረምበታለን
ለትውልድ ምስክር ልንሆንለት በቅተን ይህን እናያለን
እንደ ተስፋ ቃሉ ይመጣል
ሀሰትን አያውቅም እግዚአብሔር መች ይስታል
በእንቆቅልሽ ያለ የሚያነባው ሁሉ ቋጠሮው ይፈታ
