አንተ ብቻ ጌታ ነህ

128

አንተ ብቻ ጌታ ነህ
አንተ ብቻ ጌታ /2/ ነህ ኸኸ
አንተ ብቻ ንጉሥ /2/ የእስራኤል ቅዱስ /2/

1. በፊት ጀግና እንዳለነበረ
ዛሬ ምን ነካው አትባል /2/
በምትሠራው አትከሰስ
እግዚአብሔር ማንም ያውቅሃል /2/

ረዳት ባለሙያ አትሻም
አንተ እኮ ሁሉ አዋቂ ነህ
ለዘላለም ስምህ ይባረክ
በሥራህ ሰው ታስመካለህ /2/

ለታላቅነትህ እንከን አይወጣልህ
ማንም በአመራርህ /በአሠራርና/ አይማረርብህ
በቅን ትገዛለህ በቅን ትፈርዳለህ
በክብርህ ለመጣው መች አንተ ታንሳለህ /2/

እግዚአብሔር ቀናተኛ ነህ /3/
ለክብርህ ቀናተኛ ነህ /3/

2. ማንነቱን ላጫወተ አኸኸ
ለቀረበህ ለወደደህ አኸኸ /2/
ፍቅርህ ታለምደዋለህ አኸኸ
ምስኪኑን መች ትንቃለህ አኸኸ/2/

እንዳንተ ያለ በእውነት የት አለ
የታወቀ በአሠራህ
የከበደብንን ቀንበር ሰብሮ
የሚያረካ በማዳኑ /2/

ለታላቅነትህ እንከን አይወጣልህ
ማንም በአመራርህ /በአሠራርና/ አይማረርብህ
በቅን ትገዛለህ በቅን ትፈርዳለህ
በክብርህ ለመጣው መች አንተ ታንሳለህ /2/

እግዚአብሔር ቀናተኛ ነህ /3/
ለክብርህ ቀናተኛ ነህ /3/

3. ከሰማያት የፅድቅ ጠላት አሃሃ
ከምድሩም ባላንጣችን አኸኸ /2/
አንተ ማን አሰጋህና አሃሃ
መቼ አፈርን በምርጫችን አኸኸ/2/

እንደጥንቱ ዛሬም ኃያል ነህ
ካንተ በላይ ማንም የለም
ሳንሳቀቅ ሳንሰጋ
እንኖራለን ለዘላለም /2/

ለታላቅነትህ እንከን አይወጣልህ
ማንም በአመራርህ /በአሠራርና/ አይማረርብህ
በቅን ትገዛለህ በቅን ትፈርዳለህ
በክብርህ ለመጣው መች አንተ ታንሳለህ /2/

እግዚአብሔር ቀናተኛ ነህ /3/
ለክብርህ ቀናተኛ ነህ /3/

አንተ ብቻ ጌታ ነህ
አንተ ብቻ ጌታ /2/ ነህ ኸኸ
አንተ ብቻ ንጉሥ /2/ የእስራኤል ቅዱስ /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top