ነፍሴን አሳልፌ ፈቅጄ እሰጣለሁ
መልሼም ለመውሰድ ስልጣን አግኝቻለሁ
በሶስተኛውም ቀን ከሞት እነሳለሁ
እንዳለ አልቀረም ሞትን ድል አረገው
መቃብሩ ደጃፍ ላይ ያለው ትልቅ ቋጥኝ
እኔ አልችለውም ማን ያንከባልልኝ
እያልኩኝ ስቸገር ወደ ላይ ሳማትር
ተነሳ ኢየሱስ ፈንቅሎ መቃብር
ኦ ድል ኦ ግሩም ድንቅ ድል
ኦ ድል ኢየሱስ ሃያል
መቃብሩን ዘግተው በማህተም አሽገው
ማስጠበቅ ጀመሩ ወታደር አቁመው
ሃያሉ ኢየሱስ ግን በጊዜው ተነሳ
አልቻሉም ሊይዙት ሁሉንም ድል ነሳ
ካህናት ትንሳኤውን ሊክዱ ፈልገው
ለጠባቂዎቹ ገንዘብ ስጡዋቸው
ግን ሊያጠፉ አልቻሉም የትንሳኤውን ዝና
በአለም ተዳረሰ እጅግ ገነነና
