ተጠመቀልን

281

በበርሃ የሚጮህ ድምፅ ራሱን አይቶ ሰው እንዲያንፅ /2/
ጎባጣው ይቅና ጎድጓዳው ይደልደል
ዋግ የመታውም እንዳዲስ ያለምልም /2/

ተጠመቀልን ጌታ ተጠመቀልን
ተጠመቀልን ኢየሱስ ተጠመቀልን /2/

አርያ ሊሆን ራሱን አዋረደ ንጉስ በባርያው እጅ ተጠመቀ
የጫማውን ማሰርያ ሊነካ ያልተገባ
ዮሀንስ ከበረ ትንሽ ሆኖ ገባ /2/

በበርሀ የሚጮህ ድምፅ ራሱን አይቶ ሰው እንዲያንፅ /2/
ገለባን ከፍሬ በመንሹ ይለያል
አውድማውን ያጠራል ገለባውን ያቃጥላል /2/

በአንድ አምላክ ሶስት አካላት ሕላዌውን ላለም ሊያስተምራት
ማህያዊውን ፍቅሩን ሰጠን
በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀልን /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top