ማርያም እመቤቴ ማርያም እመቤቴ
ማርያም ውድ እናቴ ማርያም ውድ እናቴ
በእምነት ተላላነት በእሽታ ሞኝነት
አምላክ እንዲመጣ ባንቺ አየን በምነት
ከፀባኦት ወርዶ አምላክ ባንቺ አደረ
የትውልድ እፎይታ ባንቺ ላይ ሰመረ
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ለአብ ነሽ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ
በመንፈስ የከበርሽ ቅዱስ ነሽ ታቦቱ
በበረት ውስጥ ሆነሽ ዝቅ ካለው ቦታ
አምላክን ወለድሽው አንዘምር በእልልታ
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
የአዳም ተስፋው ሆይ ረጅሟ መሰላል
የሰማይ ስፋቱ ባንቺ ይመሰላል
የደህንነታችን ኪዳን መመኪያ ሆይ
ለምኝልን እንበል ዘውትር ቅድስት ሆይ
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
