ታዛዥ የሆነች

231

የአብነት የጽናት እመቤት
የፍቅር የሰላም ንግስት
የጐልጐልታ ተጓዥ ብጽእት

ማርያም ናት /3/

ታዛዥ የሆነች የአምላካችን እናት
የልጆቿ ፍቅር ሁሉ የሚያቃጥላት
የፍጥረት ንግስት እሱ የመረጣት
አማላጃችን ድንግል ማሪያም ናት አሜን /3/

በጽናት የኖረች በጌታ ፀጋ

ከሁሉ በታች ክብራን ዝቅ አድርጋ
እስከመጨረሻ ትዕግስት ያሳየች
ዛሬም ለዘለዓለም ከእኛ ጋር አለች አሜን /3/

በእምባ የተጓዘች ጐለበቷ ዝሎ
የልጆቿ ስቃይ አላስችላት ብሎ
ለእኛ አስተማረች የፍቅር ሚስጢር
ታስታርቀናለች ስሟ ይክበር አሜን /3/

ተስፋ እንዳንቆርጥ አብነት የሆነች
በቀራንዮ ስቃይ አብራ ተካፈለች
ክርስቲያኖች ሁሉ እናመስግናት
ለእመቤታችን እልል እንበልላት አሜን /3/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top